የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ዝክር መርሐ ግብር
Pyhittäjä Aleksanteri Syväriläisen kappeli Myyllpurontie 1, Helsinki, Finland+ + + በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳሌ ፲፥፯ የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸዉ ይደርብንና በየወሩ የምናከብረዉ የዝክራቸዉ መርሐ ግብር የፊታችን ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ይሆናል። መርሐ ግብሩ የዝክር መርሐ ግብር ብቻ ነው፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ ስለማይወስድ ከበረከቱ ለመሳተፍ እንድንገናኝ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ቀን ፦ ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ (Monday May 2 2016) ሰዓት፡ 18:00 – 19:00ቦታ፦ Pyhittäjä Aleksanteri Syväriläisen kappeli Myllypurontie 1, Helsinki ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ