የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ዝክር መርሐ ግብር

Pyhittäjä Aleksanteri Syväriläisen kappeli Myyllpurontie 1, Helsinki, Finland

+ + + በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳሌ ፲፥፯ የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸዉ ይደርብንና በየወሩ የምናከብረዉ የዝክራቸዉ መርሐ ግብር የፊታችን ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ይሆናል። መርሐ ግብሩ የዝክር መርሐ ግብር ብቻ ነው፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ ስለማይወስድ ከበረከቱ ለመሳተፍ እንድንገናኝ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ቀን ፦ ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ (Monday May 2 2016) ሰዓት፡ 18:00 – 19:00ቦታ፦ Pyhittäjä Aleksanteri Syväriläisen kappeli  Myllypurontie 1, Helsinki ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ

ስብረተ አፅሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ቅዳሴ

St. Alexander of Svir Chapel Jauhokuja 3, Helsinki, Finland

+ + + በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ዕለት የቅዳሴ መርሐ ግብር አዘጋጅተናል። ስለሆነም ፤ በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። የቅዳሴ መርሐ ግብር ሰዓት ፡- ከጠዋቱ 12:00 – ቀን 3:00 (6:00-9:00) ቦታ ፡- Myllypuro Jauhokuja 3 ,Helsinki ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! በስዊድንና ስካንዲናቪያ ሀገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ