የጻድቁ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽማቸው ክብረ በዓል እና ዐውደ ርእይ

Unnamed Venue Sammatintie 5, Helsinki, Finland

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። "የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው ፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጥብቃል።" መዝ 33፥19። ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቅዳሜ ግንቦት 13 2008( May 21 2016) ጠዋት ከ2 ሰዓት ጀምሮ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽማቸው ክብረ በዓል ይከበራል። በዕለቱ ቤተክርስቲያኗ በፊንላንድ የተመሠረተችበትን 5ኛ ዓመትም የሚከበር ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ልዩ ዐውደ ርእይ ተዘጋጅቷል።በዕለት ከቤተሰቦ ጋር በመሆን በቦታው ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጻድቁ ስም ተጠርታችኋል። ቀን፡- ቅዳሜ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም (May 21 2016) ሰዓት፡- 8:00 - 18:00 ቦታ፦ Sammatintie 5, Helsinki ዝርዝር መርሃግብር 1 .ከ8-10 ፥30 ኪዳንና ጸሎተ ቅዳሴ በተጋባዥ አበው 2. ከ10፥30-10፥40 መዝሙር በደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን 3.ከ10፥40-11፥20 ትምህርት ከተጋባዝ አበው 4.ከ11፥20-40 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል 5.ከ11-40-12፥00 ወረብ በደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን 6.ከ12፥00-12፥10ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ በተገኙ አበው ተሰጥቶ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል 7.ከ12፥10-14፥30 የምሣ ፕሮግራም በደብሩ በዓላትና መስተንግዶ ክፍል 8.ከ14፥30-15፥00 የዐውደ ርእይ ዝግጀት /እንግዶችን ቦታ ማስያዝ/ በዐውደ ርእይ ዝግጅት ኮሚቴ 9.ከ15፥00-15 ፥10 የዐውደ ርእይ መክፈቻ ፕሮግራም 10.ከ15፥10-18፥00። ሕዝቡ ዐውደ ርዕዩን የሚያይበት በዐውደ ርእዩ ገላጮች 11.18፥00 የዕለቱ ፕሮግራም ፍፃሜ ይሆናል። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት የክብረ በዓል

Maunulan kirkko Metsäpurontie 15, Helsinki, Finland

+ + + በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይንልገራል።"መዝ፦36፥ 30 የክብረ በዓል ጥሪ የተከበራችሁ በፊንላንድና በአጎራባች ሀገሮች የምትገኙ አድባራት አበው ካህናት ወዲያቆናት፥የሰንበት ት/ቤት መዘምራን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ !የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 22/04/2009 /Des 31.12.2016. ከዋዜማው ዐርብ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በዕለቱ ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ቀን ፡-21-23/04/2009 ዓ.ም (30-31/12/2016) ሰዓት ፡-ዐርብ ምሽት 4:30 – ቅዳሜ ቀን 12:00 (Fri 22:30- Sat 12:00) ቦታ ፡- Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa) ዝርዝር መርሃግብር ዐርብ ማታ በ21/04/2009 ከ22፥30 -01፥00 ፣ገድለ ተክለሃይማኖት ይተረጎማል ትምህርትና መዝሙር ከ01፥00-6፥00 ማኅሌት ይቆማል ከ6፥00-6፥30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል ከ6፥30-9፥00 ቅዳሴ ይከናወናል ከ9፥00-10፥00 ትምህርትና መዝሙር ከ10፥00-11፥30 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል 12፥00 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ከ12፥00-13 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ

የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት

Maunulan kirkko Metsäpurontie 15, Helsinki, Finland

+++ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። “የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።” መዝ. 36፥ 30 የተከበራችሁ በፊንላንድና በአጎራባች ሀገሮች አድባራት የምትገኙ አበው ካህናት ወዲያቆናት፥ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ! የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 21/04/2010 /Dec 30.12.2017. ከዋዜማው ዐርብ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል በመሆኑም በዕለቱ ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ዝርዝር መርሃግብር ከ22፥00 - 01፥00 ገድል ትርጉምና ስብሐተ እግዚአብሔር ይደርሳል (ዐርብ ማታ በ20/04/2010) ከ01፥00 - 06፥00 ማኅሌት ይቆማል ከ 06፥00 - 06፥30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል ከ06፥30 - 09፥00 ቅዳሴ ይከናወናል ከ09፥00 - 10፥00 ትምህርትና መዝሙር ከ10፥00 - 10፥20 ታቦተ ሕጉ ዑደት ያደርጋል ከ10፥20 - 10፥40 የደብሩ መዘምራን ወረብ ያቀርባሉ ከ10፥40 - 11፥30 ማስታወቂያዎችና መልእክቶች 12፥00 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል   ቦታ፡  Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን። http://www.teklehaymanot.fi/

በዓለ ልደቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት

Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa, Finland

+ + + በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ዕለት በዓለ ልደቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ክብረ በዓልአዘጋጅተናል። ስለሆነም ፤ በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ክብረ በዓል ሰዓት ፡- ከምሽት 3:00 – ቀን 6:00 (21:00-12:00) ቦታ ፡- Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa) ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ

ፍልሰተ አጽሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት የንግሥ ክብረ በዓል

Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa, Finland

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው ፤ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል። መዝ ፴፫፤፲፱ በዓለ ፍልሰተ አጽሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ግንቦት ፲፮ - ፲፯ / May 24 - 25 በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በነዚህ እለታት ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል። የበዓሉ ዝርዝር መርሓግብር እንደሚከተለው ቀርቧል። 22:00 - 01:00 ገድል ይተረጎማል ፣ እንዲሁም ስብከተ ወንጌል ከአዲስ አበባ በመጡ መምህር ይሰጣል። 01:00 - 05:00 ሥርዓተ ማኅሌቱ በሊቀ ጠበብት ተክሌ ሲራክ እየተመራ ከተለያዩ አድባራት በሚመጡ ሊቃውንት ይከናወናል። 05:00 - 05:30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል። 05:30 - 08:00 ጸሎተ ቅዳሴ ይከናወናል። 08:00 - 08:45 ስብከተ ወንጌል ይሰጣል። 09:00 - 10:00 ታቦተ ሕጉ ዑደት ያደርጋል። 10:00 - 10:20 በደብሩ መዘምራን ወረብ ይቀርባል። 10:20 - 10:40 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል። 10:40 - 11:00 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት

በዓለ ልደቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት

Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa, Finland

+ + + በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል ከአንደበቱም ፍርድን ይናገራል " መዝ. 36 : 30 የተከበራቹ በፊንላንድ እና አጎራባች ሀገሮች የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ምእመናን በሙሉ ታኅሣሥ 25 / 2012 ዓ.ም Jan 4 / 2020 በዓለ ልደቱ ለ አቡነ ተክለሃይማኖት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። በዕለቱ ሁላችሁም ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንድትሆኑ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ዝርዝር መርሃ ግብር  22:00 – 01:00 ትምህርት እና ስብሐተ እግዚአብሔር ይደርሳል  01:00 – 05:30 ማኅሌት ይቆማል  05:30 – 06:00 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል  06:00 – 08:30 ጸሎተ ቅዳሴ ይከናወናል  08:30 – 09:15 ትምህርተ ወንጌል  09:15 – 09:40 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል  09:40 – 10:00 የደብሩ መዘምራን በዓሉን በተመለከተ ወረብ ያቀርባሉ  10:00 – 10:15 ስለ ደብሩ ሕንጻ ቤ/ክ ግዥ እንቅስቃሴ ገለጻ  10:15 – 10:30 ቃለ ምዕዳን ተደርጎ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል  10:30 – 11:30 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዐሉ ፍጻሜ ይሆናል   ክብረ በዓል ሰዓት ፡- ከምሽት 4:00 – ቀን 6:00 (22:00-12:00) ቦታ ፡- Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa) ዝርዝር መርሃ ግብር በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ