የጻድቁ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽማቸው ክብረ በዓል እና ዐውደ ርእይ
Unnamed Venue Sammatintie 5, Helsinki, Finland††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። "የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው ፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጥብቃል።" መዝ 33፥19። ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቅዳሜ ግንቦት 13 2008( May 21 2016) ጠዋት ከ2 ሰዓት ጀምሮ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽማቸው ክብረ በዓል ይከበራል። በዕለቱ ቤተክርስቲያኗ በፊንላንድ የተመሠረተችበትን 5ኛ ዓመትም የሚከበር ሲሆን ይህንኑ አስመልክቶ ልዩ ዐውደ ርእይ ተዘጋጅቷል።በዕለት ከቤተሰቦ ጋር በመሆን በቦታው ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጻድቁ ስም ተጠርታችኋል። ቀን፡- ቅዳሜ ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም (May 21 2016) ሰዓት፡- 8:00 - 18:00 ቦታ፦ Sammatintie 5, Helsinki ዝርዝር መርሃግብር 1 .ከ8-10 ፥30 ኪዳንና ጸሎተ ቅዳሴ በተጋባዥ አበው 2. ከ10፥30-10፥40 መዝሙር በደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን 3.ከ10፥40-11፥20 ትምህርት ከተጋባዝ አበው 4.ከ11፥20-40 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል 5.ከ11-40-12፥00 ወረብ በደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን 6.ከ12፥00-12፥10ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ በተገኙ አበው ተሰጥቶ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል 7.ከ12፥10-14፥30 የምሣ ፕሮግራም በደብሩ በዓላትና መስተንግዶ ክፍል 8.ከ14፥30-15፥00 የዐውደ ርእይ ዝግጀት /እንግዶችን ቦታ ማስያዝ/ በዐውደ ርእይ ዝግጅት ኮሚቴ 9.ከ15፥00-15 ፥10 የዐውደ ርእይ መክፈቻ ፕሮግራም 10.ከ15፥10-18፥00። ሕዝቡ ዐውደ ርዕዩን የሚያይበት በዐውደ ርእዩ ገላጮች 11.18፥00 የዕለቱ ፕሮግራም ፍፃሜ ይሆናል። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!