ልዩ የልደትና የጥምቀት በዓል መርሃ ግብር በሕፃናትና አዳጊ ልጆች

Kotikirkko Adarash Unioninkatu 39, Helsinki, Finland

+++   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ”ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው” መዝ. 126(127)፥3   ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን እና የመድኃኒታችንን ልደት ምክንያት በማድረግ በዚህ ዕለት እሁድ ልዩ የሕፃናትና አዳጊ መርሃ ግብር ስላዘጋጀ ሕፃናት በሙሉ ፕሮግራሙን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዕለቱ - ሕጻናት መዝሙር ስነጽሑፍ ያቀርባሉ - ለሁሉም ሕጻናት ስጦታ ይሰጣል - በሕጻናት ዙሪያ ትምህርት እና ወንጌል ይኖራል   በዚህ ቀን ሁላችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁን ይዛችሁ በአድነት ሆነን እግዚአብሔርን እንድናመሰግን በዓሉንም እንድናከብ ጥሪ እናስተላልፋለን።   እሑድ ጥር 20 2010 ዓ.ም (January 28, 2018) ሰዓት ቀን 9:00 – ምሽት12:00 (15:00-18:00) ቦታ Siltavoudintie 12, 00640 Helsinki መልካም በዓለ ልደት ይሁንልን!!!     በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል ፊንላንድ

የኪዳን እና የምህላ ጸሎት ቀጥታ ስርጭት

Online Skype sermon for kids https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የተወደዳቹ የ እግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ። እንደሚታወቀው በአሁን ወቅት በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመንኖርበት ሀገር ከ 10 ሰው በላይ መሰብሰብ የሚከለክል ሕግ ወጥቷል። በመሆኑም የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት በርቀት ስርጭት እንድናደርግ ተገደናል። የፊታችን ቅዳሜ ቁጥራቸው ከ10 የሚያንስ ካህናት እና ዲያቆናት እንዲሁም የቀረጻ ባለሙያዎች ብቻ የሚገኙበት የ ኪዳን እና የምህላ ጸሎት መርሐግብር በቀጥታ ስርጭት Helsinki Debre Amin Abune Tekle Haymanot Church በሚለው የፌስቡክ ገጻችን በቀጥታ የሚተላለፍ በመሆኑ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በሰዓቱ በየቤታችሁ ሆናችሁ እንድትከታተሉ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ። ቀን : 04 / April / 2020 ሰዓት : ከጠዋቱ 7:00 - 8:30 ሰዓት ቦታ : Helsinki Debre Amin Abune Tekle Haymanot Church Facebook page https://www.facebook.com/eotcHelsinkiTekleHaymanot ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን መረጃና ግንኙነት ክፍል

ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች በስካይፕ ትምህርት

Online Skype sermon for kids https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO

+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ። ኢሳ. ፳፮፥፳ ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንደሚታወቀው ዓለምን እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ የዓለም መነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰንብቷል። የፊንላንድ መንግሥትም ከ10 ሰው በላይ በአካል ሕዝብ መሰባሰብ እንደማይቻል አዋጅ አውጇል። በዚህ መሠረት በቤተ ክርስቲያናችንም መደበኛ መርሃ ግብር ማድረግ ስለማይቻል ሁላችንም በያለንበት እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቅ እያልን፤ በደብራችን የወላጆች ኮሚቴ ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ አዳጊ ልጆች እሑድ እሑድ ጠዋት ከ10:00 – 11:00 ሰዓት ድረስ በስካይፕ ትምህርት መዘጋጀቱን ለማሳወቅ እንወዳለን። ስለሆነም ከ7 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ያላችሁ ወላጆች ልጆቻችሁ በዚህ የስካይፕ አድራሻ https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO በመግባት ትምህርቱን እንዲከታተሉ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን። ለመርሃ ግብሩ መሳካት ተሳታፊዎች በሰዓቱ እንድትገቡ ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ምናልባት በተላከው ሊንክ መግባት ካልቻላችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር 0456987878 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ። ትምህርቱ በዚህ ሳምንት እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም (22.3.2020) በተጠቀሰው ሰዓት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን። ቀን : ዘወትር እሑድ ሰዓት : ጠዋት ከ10:00 – 11:00 ሰዓት (በ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ጠዋት ከ 4 :00-5:00 ሰዓት) የስካይፕ አድራሻ : https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ። ዘጸ. ፲፭፥፳፮ እግዚአብሔር በአገልግሎት ያበርታን። በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በስዊድን እና ስካንዲኔቪያን ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል ፊንላንድ

ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች በስካይፕ ትምህርት

Online Skype sermon for kids https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ! የዚህ ሳምንት መደበኛ መርሃ ግብራችን ጠዋት 10:00 ሰዓት የሚጀመር መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። ዝርዝር መርሃ ግብሩም ከዚህ በታች እንደተጠቀሰው ይሆናል። 1. ከ10:00 - 10:05 መርሃ ግብሩን በጸሎት መጀመር 2. ከ10:05 - 10:10 መዝሙር (አንትሙሰ ንበሩ / ሐና ኤንጌርቮ) 3. ከ10:10 - 10:15 ሥነ ጽሑፍ (ብሩክታዊት) 4. ከ10:15 - 10:20 መዝሙር (ማርያም ፊደል / ሔመን አምሐ)) 5. ከ10:20 - 10:50 ትምህርት (ዲን. ዓለምነው) 6. ከ10:50 - 10:55 መዝሙር (ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት / የአብ ቡሩክ) 7. ከ10:55 - 11:00 መርሃ ግብሩን በጸሎት መፈጸም መርሃ ግብራችን እንደ ነባራዊ ሁኔታ ሊቀያየር ይችላል።