ትምህርተ ሃይማኖት


07
Apr 2016
ጸሎት ክፍል 1

በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡ ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣ ሰው......

Read More


07
Apr 2016

በዲ/ን ኅብረት የሺጥላ ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡ ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል......

Read More


07
Apr 2016
ዳግም ምጽአት

ዳግም ምጽአት ‹‹ደገመ›› እና ‹‹መጽአ›› ከሚሉ ሁለት የግዕዝ ግሦች የተዋቀረ ሐረግ ነው፡፡ የጌታችንንና የአምላካችንን ለሁለተኛ ጊዜ ወደዚህች ዓለም መምጣት ያመለክታል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ዳግምነቱ ለልደቱ ነው፡፡ ማለትም ልደቱን ‹‹ቀዳማዊ ምጽአት›› ካልን ዘንድ ለፍርድ መምጣቱን ‹‹ዳግም ምጽአት›› እንላለን፡፡ ‹‹ዳግም›› የሚለውን ቃል አንድ ነገር ያለ ምንም ለውጥ ወይም ልዩነት ሲደገም የምንጠቀምበት ከሆነ ‹‹የተካከለ ዳግም›› እንለዋለን፡፡ ያ ነገር መሠረታዊ ጭብጡን ሳይለቅ ነገር ግን በበርካታ ለውጦች ታጅቦ ከተደገመ ወይም ከቀደመው ጋር ሲነጻጸር ተደገመ የሚያሰኝ ምሥጢራዊ አካሄድ ካለው ‹‹ያልተካከለ ዳግም›› ይባላል፡፡ ፍጹም የሆነ መመሳሰል የሌለው መደገም እንደማለት ነው፡፡ ዳግም ምጽአት፣ ዳግም ልደት፣ ዳግም ትንሣኤ ወዘተ ‹‹ያልተካከለ ዳግም››......

Read More