17
Jun 2019
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የቆየው መንፈሳዊ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ልዩ ጉባኤ ተካሄዷል ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር መጋቤ ሐዲስ በሙሉ አስፋው መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን ጨምረው በንስሐ ሕይወት እና በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል ። ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የማኅበረቅዱሳን በአዉሮፖ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ መንፈሳዊ መዝሙሮች እና ሥነጽሑፍ በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ቀርቧል ። በርካታ......
Read More
16
May 2019
በፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በጋራ የተዘጋጀው ልዩ ዐውደ ጥናት ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 3 2011 ዓ.ም (May 11 2019) በፊንላንድ ሄልሲንኪ በሚገኘው ሶፊያ የባህል ማዕከል በርካታ ምእመናን እና ታዳሚዎች በተገኙበት ተካሄዷል :: ለሦስተኛ ጊዜ በተዘጋጀው እና ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥናታዊ ጽሑፎች በአንድ ኢትዮጵያዊ እና በሦስት ፊንላንዳውያን ሙሑራን ቀርቧል ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ በቀዳሚነት በዲያቆን አረጋ ጌታነህ ቀርቦ ግንዛቤ አስጨብጧል። ለረጅም ዓመታት የፊንላንድ ሉተራን ቤተክርስቲያን አለቃ የነበሩት ኒሎ ሆንካነን በነገረ ማርያም ዙሪያ በተለይ ማኅሌተ ጽጌን በተመለከተ......
Read More
19
Mar 2019
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አውሮጳ መንበረ ጵጵስናው ስዊድን ስቶኮሆልም የሆነ ሀገረ ስብከት ተመሠረተ ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አሠርተ ዓመታት ያህል በአስተዳደር ተከፍላ ብትቆይም በሐምሌ 2010 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሕደቱ ከተፈጸመ በኋላ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት አውሮጳን ለዐራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል መወሰኑ ይታወቃል ። በዚህ መሠረት በስዊድንና እስካንድንቢያን ሀገሮች እራሱን ችሎ አንድ ሀገረ ስብከት እንዲሆንና በአንጋፋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እንዲመራ በመወሰን የተነሳ መጋቢት 6 እና 7 /2011 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናው ስቶኮሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት ምሥረታው......
Read More
22
Jan 2019
ከሲኖዶሳዊ ዕርቅና ሰላም በኋላ የመጀመሪያው በዓለ ጥምቀት በሰሜን አውሮፓ በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ÷ ጥር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በጋራ ተከበረ፡፡ የበዓሉ የአከባበር ሥነ ሥርዐት እና ጸሎተ ቅዳሴው በደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያ አስተዳዳሪ ÷ በመልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ እየተመራ ÷ከተለያዩ የፊንላንድ ከተሞች የመጡ ኦርቶዶክሳውያን በተገኙበት በጸሎተ ቅዳሴና በትምህርተ ወንጌል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በተዘጋጀው የባሕረ ጥምቀት ሥፍራ ስብሐተ እግዚአብሔር ደርሶ፣በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ዕለቱን የሚያዘክር ወረብ ቀርቦና ከኢትዮጵያ በመጡት መምህር ÷በዲያቆን ታደሰ ወርቁ በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ከተሰጠ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ ከዚሁ ጋራ......
Read More
17
Dec 2018
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ሁለት ዓመታትየሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ አካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አውሮጳ በስዊድንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም (16.12.2018 ) ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ከ2019 – 2020 ዓ.ም የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤአባላት ምርጫ አካሄዷል፡፡ለሁለት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያገለግሉ አባላትን ለመምረጥ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም (3.11.2018) በአጥቢያው ምእመን ሶስት አባላት ያለው የአስመራጭ ኮሚቴ ተመርጦ የምርጫ ሂደቱን ተከናውኗል። በሐምሌ ወር 2010 ዓ•ም በአስተዳደር ለሁለት ተከፍሎ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነትን ተከትሎ......
Read More
24
Sep 2018
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 12 – 13 ቀን 2011 ዓ.ም ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው ላይም የአውሮፓ አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ቀዳማዊ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ካህናት፤ ከመላው ፊንላንድ የተሰባሰቡ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተገኝተዋል። ጉባኤው ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ጠዋት በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ በጸሎተ ቅዳሴ ተጀምሯል። የአንድነት ጉባኤውን ለማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መከፋፈል ምክንያት ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን በፊንላንድ የሚኖሩ ምዕመናን......
Read More
09
Sep 2018
አዲሱ ዓመት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ......
Read More
30
Jul 2018
የተላኩብፁዓን አባቶች፣የተደረሰበትን ስምምነት የሚያስረዳ መግለጫ ለጉባኤው አቀረቡ፤ የነበረው የአባቶች መለያየት ለውግዘት በሚዳርግ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር የታወቀ ነው፤ የተደከመበት ዕርቀ ሰላም ለውጤት በመብቃቱ በስምምነቱ መሠረት ውግዘቱ ተነሥቶአል፤ የጳጉሜ 1984፣ የመስከረም 1985፣ የጥር 1999ዓ.ም.ቃለ ውግዘት፣ከዛሬ ጀምሮ ተነሥቶአል፤ ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትንና ከልዩነት በኋላ የተሾሙትን ተቀብሏቸዋል፤ ††† ስያሜያቸው እንዳለ እንደተጠበቀ፣በውጭ ሀገርም ኾነ በሀገር ቤት ተመድበው ያገለግላሉ፤ ከ1-6 ተራቁጥር የተዘረዘሩትን የዕርቀ ሰላም ነጥቦች ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቋል፤ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና የሀገር ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የበኩሉን ይፈጽማል፤ ጠ/ሚሩ፣ ችግሩ የሀገርም መኾኑን በመገንዘብ አስተጋባኢና አሰባሳቢ መመሪያ ሰጥተዋል፤ ብዙ የተደከመበት ጉዳይ ፈጣን መፍትሔ እንዲያገኝ ስላደረጉ ልባዊ ምስጋና ያቀርባል:: ††† ምንጭ: ሐራ ዘተዋሕዶ...
Read More
29
Jul 2018
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ልኡካን አባቶች ረቡዕ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፤ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ በመጪው መስከረም ለመመለስ ቢያስቡም፣ በጠ/ሚሩ ጥሪ አሳጠሩት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴ ዝግጅቱን እያጣደፈ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ፣ ከ17 በላይ የተሟሉ ማረፊያዎች ተዘጋጁ፤ ይፋዊ የአቀባበል መርሐ ግብሩ፣ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፤ “ለመቀበል እየተዘጋጀን ነው፤ታላቅ ደስታ ነው፤”/ብፁዕ ዋና ሥ/አስኪያጁ/ ††† የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ አንድነት በአባቶች ዕርቀ ሰላም መመለሱን ተከትሎ፣ ላለፉት 26 ዓመታት በአሜሪካ በስደት የቆዩት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በመጪው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው......
Read More
27
Jul 2018
ሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ልኡካን አባቶች ስምምነት ዝርዝር: ኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች በእኩል የአባትነት ክብር ያገለግላሉ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ትመራለች፤ 4ኛው ፓትርያርክ በጸሎት እና በቡራኬ፣ 6ኛው ፓትርያርክ በአስተዳደር ሥራ፤ የኹለቱም ስም፣ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ዓለም ሁሉ ዘወትር በጸሎት ይነሣል፤ ሰማዕቱ አቡነ ቴዎፍሎስ ለሞት ከተላለፉበት ጀምሮ የቀኖና ጥሰት ተፈጽሟል፤ ቅ/ሲኖዶስ፣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር ባለማስጠበቁ ልጆቿን ይቅርታ ይጠይቃል፤ ††† ጥሰቱን ለመከላከልና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ፣ቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ ያዘጋጃል፤ በኹለቱም ሲኖዶስ የተላለፈው ቃለ ውግዘት፣ በጋራ ምልዓተ ጉባኤ ይፈታል፤ ከልዩነት በኋላ የተሾሙ ቅቡል ናቸው፤አጠራራቸው እንደ ቅደመ ተከተላቸው፤ ለውጭ ቤተ ክርስቲያን፣የየሀገሩን ሕገ መንግሥት ያገናዘበ መመሪያ ይወጣል፤ የስምምነቱን ተግባራዊነትና......
Read More