29
Sep 2022
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ። በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ካህናት እና ምእመናን ከመላዋ ፊንላንድ የመጡ በአንድነት በቦታው ተገኝተዋል።በተጨማሪም በክብር እንግድነትም የሂልሲንኪ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ላዛርዩስ ተገኝተው ለሕዝበ ክርስቲያኑ መልእክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ አንገሶም ዕቁባይ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ደመራው ተለኩሶ ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ዝማሬ ዘምረው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።...
Read More
21
Aug 2022
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት......
Read More
25
Jul 2021
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ። በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ ። በዕለቱም በመርሐግብሩ የታደሙት ምእመናን ወ/ሮ አለማች በሀገረ ፊንላንድ በስደት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ያዘነውን በማጽናናት ፣ በመጠየቅ የሀገረ ፊንላንድንም ሥርዓተ ሀገሩንም በማለማመድ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረዋል ። ወ/ሮ አለማች በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከታላቁ ካህን አባታቸውና ከለጋሷ እናታቸው የወረሱትን በጎ ተግባር ስደቱ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን......
Read More
26
Dec 2020
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ በደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላ ምርጫን አካሄዷል። ጠቅላላ ጉባኤውን በጸሎት ክፍተው የመሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የዕለቱን አጀንዳዎች ማለትም የደብሩን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ የ2021 በጀት ዓመት ማጽደቅ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ማከናወን መሆናቸውን ገልጠዋል ። የጠቅላላ ጉባኤ የምርጫው......
Read More
14
Sep 2020
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት ክብረ በዓል ነሐሴ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ተከበረ። በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ተገኝተዋል። በዓሉ ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት የጻድቁን ገድል በመተርጎም የተጀመረ ሲሆን፤ ከመንፈቀ ሌሊት ጀምሮ ማኅሌት ተቋሟል። ከማኅሌቱ በመቀጠል እሑድ ጠዋት የቅዳሴ ጸሎት ከተከናወነ በኋላ በዓሉ አስመልክቶ በደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ ትምህርት ተስጥቷል። በትምህረቱም ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ ባስተላለፉት መልእክት የጻድቁ አቡነ ተክለ......
Read More
26
Aug 2020
በፊላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ። የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር ጥቅምት 1/2012 ዓ ም የተቋቋመ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ( 22/8/2020 ) Tuomiokirkokatu 27 ላይ በሚገኘው የፊላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅዳሴው አገልግሎት የተመራው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ እንዲሁም በፊላንድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ሰላም መድኅንያዓለም ቤተክርስቲያን ምክትል አስተዳዳሪ ቀሲስ አንገሶም ዲያቆናት አማካኝነት የተፈጸመ ሲሆን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን እንዲሁም ከፊላንድ ከተለያየ......
Read More
04
Aug 2020
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የተጋጀው ልዩ የልጆችና የወላጆች መርሐ ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ተካሄደ! በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ልዩ የልጆችና የወላጆች መርሐ ግብር ቅዳሜ ሐምሌ 25/11/2012 በሰሜናዊ ሄልስንኪ በተለምዶ ሃጋ አካባቢ በሚገኘው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ተከናውኗል። በአይነቱ ልዩ የሆነው የልጆች እና የወላጆች መርሐ ግብርን በጸሎትና ያስጀመሩት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ነበሩ። በመቀጠልም መርሐ ግብሩን ያዘጋጁት በጽጌ......
Read More
26
Apr 2020
በስዊድንና እስካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው በኮረና ቫይረስ እየቀጠፈ ያለው ሕዝብ በዝርወት ከሚከኙት መካከል ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ተጠቃሾች መሆናቸው የሚታወቅ በመሆኑ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት በሥሯ አገልግሎት የሚያገኙትን በመላዋ ፊንላንድ የሚገኙትን ምእመናንን ጤንነት እና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የመረዳዳት በጎ ተግባር የሚያስተባብር ኮሚቴ ማዋቀሯን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለማ በሱፍቃድ ገለጹ፡፡ ኮሚቴው የአጥቢያው ምእመናን በዚህ ቫይረስ ቢያዙ እንኳን አስፈላጊውን ማኅበራዊ ሥነ ልቡናዊና ተመሳሳይ እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚያስተባብር ተጠቁሟል ፡፡ ኮሚቴው ከሄልሲንኪ ውጪ ባሉት ምእመናን ባሉባቸው ከተሞችም የመረዳዳት አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርግበትን አቅጣጫም ማስቀመጡን ታውቋል፡፡......
Read More
21
Jan 2020
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ጥር 11 /አሥራ አንድ የሚከበረው የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በተለየ ሃይማኖታዊ ድምቀት ተከብሯል። የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) መመዝገቡን ተከትሎ ዘንድሮ ሥርዓቱን በጠበቀና በደመቀ መልኩ ታቦተ ሕጉ በምእመናን ታጅቦ ከበዓሉ ዋዜማ በሚከበረው የከተራ በዓል ጊዜያዊ ማረፊያው ጉዞ አድርጎል:: ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ድምቀት የተጀመረው የጥምቀት በዓሉ ሌሊቱን በካህናቱ አገልግሎት አድሮ ከሌሊቱ 10 /አሥር ሰዓት/ ጀምሮ የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ቀጥሏል። የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ ባሕረ ጥምቀቱ ተባርኮ ሕዝበ ክርስቲያኑም ጠበል ተረጭቷል። የደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ቀሲስ......
Read More
29
Aug 2019
በስዊድንና እካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዓለ እረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ነሐሴ 18 እና 19/2011 ዓ.ም በድማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ። በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተገኙ ሲሆን ሌሎችም ከ አውሮጳ ከተለያዩ አድባራት የተጋበዙ ሊቃውንትም በበዓሉ ተገኝተዋል ። ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ከበዓሉ ቀደም ብለው ሄልሲንኪ የገቡ ሲሆን ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ጋር የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርትሲያን ለቤተ ክርስቲያናችን እስካሁን ላደረገችውና እያደረገች ላለው ትብብር አመስግነዋል። ወደፊትም ለአስፈላጊው አገልግሎት ሁሉ እንዲተባበሩ ጥሪ ከማቅረባቸው በተጨማሪም የጋራ በሆኑ አገልግሎቶች ተባብሮ መሥራትን በተመለከተ በማንሳት ውይይት አድርገዋል ።......
Read More